
የመጀመሪያ ዙር አዲስ መሶብ እንዲገቡ የተመረጡ13ቱ ተቋማት በመሶብ የአንድ አገልግሎት ማዕከልን አገልግሎት የሚሰጡበት አግባብ ተጎበኘ
ITDB፦ ሰኔ 26/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የመጀመሪያ ዙር በአዲስ መሶብ ዋና ዋና አገልግሎቶችን ይዞ እንዲገቡ የተመረጡ13ቱ ተቋማት የIT ዳይሬክተሮችና የሶፍት ዌር ባለሙያዎች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ጎበኙ። ጉብኝቱ የተካሄደው ከተቋሙ ልምድ ለመቅሰም ሲሆን በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ዳይሬክተር ጀኔራል አቶ አንተነህ ማሞ ስለ ተቋሙ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸው የመሶብ ምንነትን፣ ስራው አጀማመር፣ አላማውም የመንግስት ተቋማትን አንድ አድርጎ በማቀናጀት በአንድ ማዕከል ውስጥ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ለማድረግ እንደሆነና መጀመሪያ በ12 ተቋማት የሚሰጡትን 41 አገልግሎቶችን ይዞ ወደ ስራ እንደገባ ገልፀዋል። አሁን ላይ ብዙ ተቋማት አገልግሎታችውን በብዛት ወደ መሶብ እያስገቡ እንደሆነም ይሄውም ተቋማት ስለአገልግሎቱ ያላቸው አመለካከት በጣም እየተሻሻለ መምጣቱን የሚያሳይ መሆኑን በማመላከት የመሶብ አገልግሎት የደንበኞችን ድካም የሚቀንስ፣ ጊዜን የሚቆጥብ መሆኑን ገልፀው በእስካሁን አገልግሎታቸው ከ30.000 ደንበኞች መስተናገዳችው፣ እንደመሶብ ደግሞ 91.75% የተጠቃሚ እርካታ መኖሩን፣ እንደሃገርም ኢትዮጵያ INDEX ውስጥ አለመግባቷንና አሁን ግን አገልግሎቱ እውቅናን እያስገኘላት እንደሆነ ገልፀዋል።
ከዚህም በተጨማሪ በየክፍሉ የሚሰጡትን አገልግሎቶችን ያስረዱ ሲሆን ማንኛውም አገልግሎት ፈልጎ የሚመጣ ደንበኛ ሁሉ ተገልግሎ እንደሚመልስም ተናግረዋል። በመጨረሻም አገልግሎ አሰጣጡ ላይ መሰረት ያደረገ ጥያቄዎች የተጠየቁ ሲሆን አቶ አንተነህ ምላሽ ሰጥተውባቸዋል። በተያያዘም ጎብኚው ቡድን በአራዳ ክፍለ ከተማ እየተገነባ ያለውን የመሶብ እንድ አገልግሎት ማዕከልን ጎብኝቷል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments