
ከማዕከል እስከ ክፍለ ከተማ ያሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ባለሙያዎች በየፈተና ጣቢያዎች ሙያዊ እገዛ እያደረጉ ይገኛሉ
ITDB፦ ሰኔ 24/2017 ዓ.ም
በበይነ መረብ (on-line) እየተሰጠ ያለው የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ሁለተኛ ቀን በመልካም ሁኔታ እየተሰጠ ይገኛል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የመፈተኛ ጣቢያዎች የኢንተርኔት እና ሌሎች ለፈተና የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶች በአግባቡ አገልግሎት እንዲሰጡ እየሰራ ሲሆን የቢሮ የክላውድና ዳታ ሴንተር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ የኔጌጥ በለጠ የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ መሠረተ ልማቶችን በማሟላት የመፈተኛ ጣቢያዎችን የኔትወርክ ኮኔክቲቪቲያቸውን ዝግጁ ማድረግ በተለይ የአድዋንና የአብርሆት የመፈተኛ ጣቢያዎችን ሙሉ በሙሉ ኔት ዎርክ ዝርጋታ እና የእንታሌሺን ስራዎችን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ መስራቱን ገልፀዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከማዕከል ጀምሮ እስከ ክፍለ ከተማ ድረስ በመዋቅር ያሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ባለሙያዎች በየፈተና ጣቢያዎች በመገኘት ሙያዊ እገዛ እያደረጉ መሆናቸውን ተመላክቷል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments