
የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር
ITDB፦ ሰኔ 23/2017ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሳምንታዊው የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተከናወነ።
በዚህ መርሃ ግብር ላይ አቶ ሃብቱ አራብሴ የዕቅድና በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በዕቅድና ሪፖርት አዘገጃጀት ላይ የዕውቀት ሽግግር አድርገዋል። የዕቅድና ሪፖርት ምንነት፣ አስፈላጊነታቸው፣ ማን ማዘጋጀት እንዳለበት፣ እንዴት መዘጋጀት እንዳለባቸው፣ በምን ጊዜ መዘጋጀት እንዳለባቸው እንዲሁም በዕቅድና ሪፖርት አዘገጃጀት ላይ ስለሚስተዋሉ ችግሮች አቶ ሃብቱ በስፋት ማብራርያ ሰጥተዋል። በቀረበው ማብራሪያ ላይ ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን ለጥያቄዎቹ ምላሽ በመስጠት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments