
ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ “የአዲስ መሶብ” ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መስጠት የሚችል ማዕከል በማደራጀት ላይ ነዉ
ITDB፦ ሰኔ 17/2016 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የተቋማትን ሁለንተናዊ አቅም ለማሳደግ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል። በመሆኑም የከተማዋን አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጠፋና ዘመናዊ ለማድረግ እንዲሁም የከተማዋን ነዋሪ ኑሮ እና አኗኗር ዘመናዊ እና ለነዋሪዎችዋ እና ጎብኘዎች ምቹ ከተማ ለማድረግ የስማርት ሲቲ ስትራቴጂ ነድፎ ወደ ስራ ከገባ ሁለት አመት ሆኖታል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “የአዲስ መሶብ” ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ከአጋር ተቋማት በመገንባት እና በማደራጀት ለህብረተሰቡ ምቹ፣ ቀልጣፋ፣ ተደራሽ እና ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት የሚችል ማዕከል ለማደራጀት ስራዎች ተጀምረዋል።
የዚህ ፕሮጀክት ዋና ዓላማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመጀመሪያ ዙር የአዲስ መሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለሚገቡት 13ቱ ተቋማት የICT መሰረተ ልማታቸዉ ያለበትን ችግር በመቅረፍ እና ወሳኝ የሆኑትን ሲስተም ሶፍትዌሮችን በተለይም አዲስ መሶብ ውስጥ እንዲገቡ የተመረጡ 107 አገልግሎቶች በኦንላይን መጠቀም እንዲቻል ማድረግ ነዉ።
በመሆኑም 13ቱ ተቋማት በመጀመሪያ ዙር አዲስ መሶዉ ዉስጥ የተወሰነ ዋና ዋና አገልግሎቶችን ይዞ እንዲገቡ የተመረጡ ሲሆን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከINSA, EAII, MINT ጋር በመተባበር የተቋማት ICT መሰረተ ልማት እና ወሳኝ የሆኑት ሲስተም ሶፍትዌሮችን ከየተቋማቱ ከመጡ የIT ዳይሬክተሮችና የሶፋትዌር ባለሙያዎች ጋር በመሆን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ባመቻቸዉ ምቹ የስራ ቦታ ወደ ስራ የማስገባት ተግባር እየተከናወነ ይገኛል።
በመሆኑም እየተተገበሩ ካሉ ዋና ዋና ተግባራት መካከል፦ ከቢሮ ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር በመሆን የተቋማት የICT መሰረተ ልማቶች መፈተሽና እክል ያለባቸዉን ለይተዉ ማስተካከያ ማድረግ፣ ተቋማት እየተጠቀሙ ያሉትን ሲስተሞችን የመለየትና በተለያየ ችግር ሙሉ በሙሉ ያልተተገበሩ ካሉ እንደ አስፈላጊነታቸዉ ማስተካከያ ተደርጎላቸዉ ወደ ስራ ማስገባት ሲሆን ይህ የተጀመረው ተግባር ዘርፈ ብዙ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እና እንዲሁም በከተማ አስተዳደሩ አገልግሎት አሰጣጥ እና የተገልጋይ እርካታ ላይ የጎላ ለውጥ እንዲያመጣ የሚጠበቅ በመሆኑ በቢሮ አመራሮች ተገቢዉን ድጋፍና ክትትል እየተደረገበት ይገኛል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የተቋማትን ሲስተሞች አስፈላጊ ከሆኑት ከሌሎች ሲስተሞች እና ከኦንላይን ክፍያ ሲስተሞች ጋር ማስተሳሰር ስራ እየተከናወነ ሲሆን
አዲስ መሶብ ስራ ለመስራት ከተመረጠ አማካሪ ድርጂት ጋር በመነጋገር የICT መሰረተ ልማት
ልየታ እና ስፔስፍኬሽን በጋራ በመወሰን ከሚመለከታቸዉ ተቋማት ጋር የስምምነት ሰነድ (MOU) የመፈራረም ስራ ይከናወናል።
በመጨረሻም የዚህ ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዮናስ ደምሰዉ አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዉስጥ የተካተቱ ተቋማት የተመረጡበት አንዱና ዋናዉ መስፈርት በርካታ ተገልጋይ ያላቸዉ መሆናቸዉን ገልፀዉ በዚህ አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ አማካኝነት ተገልጋዮችን ከእንግልት የሚያወጣና ምንም አይነት የደህንነት ስጋት የሌለበት ፈጣናና ሁሉን አቀፍ ፍትሀዊ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ፕሮጀክት መሆኑን አመላክተዋል። በመሆኑም ይህ ተግባር እንደመነሻ በማድረግ ቀጣይ መሰል ተግባር እንደሚከናወን ገልፀዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments