
ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በበይነ መረብ በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የመፈተኛ ጣቢያዎች የኢንተርኔት እና ሌሎች ለፈተና የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶች በአግባቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ተገቢዉን ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ ላይ ነዉ
ITDB፦ ሰኔ 17/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ተማሪዎች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሙከራ ፈተና በመሰጠት ላይ ይገኛል።
በመሆኑም በዛሬዉ ዕለት ለተፈጥሮ ሳይንስ የትምርት መስክ ተማሪዎች በጠዋትና በከሰዓት መርሃ ግብር በሚሰጠዉ የሙከራ ፈተና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የመፈተኛ ጣቢያዎች የኢንተርኔት እና ሌሎች ለፈተና የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶች በአግባቡ አገልግሎት እንዲሰጡ የቢሮ አመራርና ከፍተኛ ባለሙያዎች ተገቢዉን ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ የማይተካ ሚናን በአግባቡ እየተወጡ ይገኛሉ።
በመሆኑም የሙከራ ፈተና ሲወስዱ አግኝተን ያነጋገርናቸው ተፈታኝ ተማሪዎች ከዋናው ፈተና አስቀድሞ የሙከራ ጊዜ መኖሩ እራስን በተገቢው መንገድ ለማዘጋጀትና ተረጋግቶ ለመስራት ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር መሆኑን ገልፀዉ ብዥታን የሚፈጥሩ አንዳንድ ነገሮች ሲኖሩ በተቆጣጣሪዎች አማካኝነት የማጥራት ስራ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።
አዲስ አበባ ከተማን ስማርት ሲቲ ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ዉጤታማ ለማድረግ ፈተናዉ በበይነ መረብ መሰጠቱ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ በመታገዝ ዉጤታማ እንዲሆኑ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments