
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ቀጣይ 90ቀናት ሥራዎች ዕቅድ ቀረበ
ITDB፦ ሰኔ 16/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የመጡትን ተጨባጭ ለዉጦች በማስቀጠል በመጭው ክረምት የንቅናቄ ስራዎችን አቅዶ መንቀሳቀስ አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን ለማስፈፀም የሚያስችል የቀጣይ 90ቀናት (ከሰኔ 5-ጳጉሜ 5ቀን 2017ዓ.ም) ስራዎች ዕቅድ ተዘጋጅቷል።
ይህም ዕቅድ ቢሮ እና ስሩ ባሉ ተጠሪ ተቋማት በዘጠና ቀናት ዉስጥ የሚከናወኑ የጥንቃቄ ተግባራት በስኬት ለማከናወን ነዉ። በዚህም መሰረት ዕቅዱን ያቀረቡት የዕቅድና በጀት ዳይሬክተር አቶ ሀብቱ አርብሴ የንቅናቄ ዕቅዱ ዋና ዋና ግቦችና ዝርዝር ተግባራት ላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ከዝርዝር ተግባራት መካከል ለአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብና አዲስ ችግኞችን መትከል፣ የክረምት የበጎ ፈቃድ ስራዎች ማከናወን፣ የኑሮ ዉድነት መቀነስና የንግድ ስርአት መግራት፣ የኮሪደር ልማት ስራ፣ የቴክኖሎጂ ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ማስመረቅ በተቀናጀ የህብረተሰብ ተሳትፎ የሰላም ግንባታ ስራ ማጠናከር፣ የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን የሚያሻሽሉ ሲስተሞች ለገቢ ሰብሳቢ ተቋማት ተደራሽ ማድረግ፣ በአገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር ስር ላይ እምርታ ማምጣት የሚችሉ የቴክኖሎጂ ዉጤቶችን ተግባራዊ ማድረግ፣ የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ማጠቃለያ ግምገማ ማከናወን፣ የፍይዳ ምዝገባ ዕቅድ ማሳካት፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄው ስራዎችን ማከናወን፣ ለብሔራዊ,ሀይማኖታዊ, እና ባህላዊ ኩነቶች ቅድመ ዝግጅት ማከናወንና የኮምንኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ስራ በጠንካራ አመራር መምራት ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።
በመጨረሻም በቀረበው ዕቅድ ላይ መሰረት ያደረገ ዉይይት በማካሄድና የተቋሙ ሰራተኞች በቀረበዉ ዕቅድ ላይ ሙሉ በሙሉ መስማማቱን የገለፀ ሲሆን የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ ማጠቃለያ በመስጠት መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments