የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖ...

image description
- In Training    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን እያስለማ ባለዉ ሲስተም ላይ መሰረት ያደረገ ዉይይት ተካሄደ

ITDB፦ ሰኔ/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን እያስለማ ባለዉ ሲስተም ላይ መሰረት ያደረገ ዉይይት ተካሄደ። በዉይይቱም ከተነሱ ዋና ዋና ሀሳቦች መካከል የትራፊክ ቅጣት አማራጭ የክፍያ ስርዓት ጋር የማቀናጀት ስራ እንዲከወን፣ የመቆጣጠር ማዕከል በተገቢው መንገድ ወደተግባር ለማስገባት ቴክኒካል እገዛን እንደሚሻ፣ ለሰርቨር ሩም የተመቻቸ ሁኔታ ከመፍጠር አንፃር እና የወረቀት አሰራር ስርዓት ለማስቀረት የሚያስችል የስማርት ኦፊስ ሲስተም እንዲለማላቸዉ እንደሚፈልጉ አመላክተዋል።

በተያያዘም የቢሮ ስማርት ሲቲ ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን ከስማርት ሲቲ ስድስት አምዶች ስማርት ሞቢሊቲ አንዱ መሆኑን ገልፀዉ ቢሮዉ ለዘርፉ ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግና እየለማ ያለዉን ሲስተም ሙሉ ለሙሉ አጠናቆ ለማስረከብ የሚያስፈልገዉን ቅድመ ሁኔታ ገልፀዋል።

በመጨረሻም የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ ሲስተሙነ ሙሉ ለሙሉ ለማስረከብ ባለስልጣን መስርያ ቤቱ አስፈላጊ እና መካተት ያለባቸው መረጃዎች መስጠት እንዳለበት እና ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ የሙከራ ትግበራ በማካሄድና በቂ የሆነ ስልጠና በመስጠት ሙሉ በሙሉ እንደሚረከቡ በማመላከት ቀጣይ መሰል ስራዎች በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments