
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ቄራ መስጅድ ጀርባ ለ16 አቅመ ደካማ አባወራ እየተሰራ ያለዉ G+3 መኖርያ ቤት የደረሰበት ደረጃ ተጎበኘ
ITDB፦ሰኔ 14/2017 ዓ/ም
በጉብኝቱ መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክንሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አዋሌ መሐመድ እና የስትራቴጂክ ካውንስል አባላት የተገኙ ሲሆን የቂርቆስ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር ዶ/ር አዲሱ ሻንቆን ጨምሮ የቂርቆስ ክ/ከተማ ምክር ቤት አባላትም በመገኘት የመስክ ምልከታ አድርገዋል።
በመስክ ምልከታ ወቅት ህንጻውን እየገነባ ያለው ጉኡሽ ካህሳይ ጠቅላላ የስራ ተቋራጭ የህንጻ ስራው የደረሰበትን ደረጃ ለጎብኝዎች ያስረዱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የህንጻው አፈጻጸም 70% መድረሱን አስረድተዋል።
በተጨማሪም በመስክ ምልከታው ላይ የፋይናንስ ድጋፍ ከሚያደርጉ የቴክኖሎጂ ካምፓኒ ባለቤቶች ተገኝተው የሚያዋጡት ገንዘብ በአግባቡ ስራ ላይ እየዋለ መሆኑን የተመለከቱ ሲሆን በቀጣይም ድጋፋቸዉን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።
በመጨረሻም የህንጻው የመጀመሪያው ወለል በፍጥነት ተጠናቆ ሸራ ውስጥ የተጠለሉት 4 ቤተሰቦችን በፍጥነት የማስገባት ስራ እንዲሰራ ክቡር አቶ አዋሌ መሐመድ አቅጣጫ በማስቀመጥ ያለው አጠቃላይ ስራ በጥሩ ሁኔታ እየሔደ መሆኑን ለምክር ቤቱ አባላት አስረድተዋል።
በተያያዘም የቂርቆስ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር አድሱ ሻንቆ የህንጻ ግንባታ በአሁን ወቅት በተሻለ ትኩረትና ክትትል እየተሰራ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ክ/ከተማውም የህንጻውን ግንባታ በተገቢዉ መንገድ ክትትል የሚያደርግ መሆኑን አንስተው በዚህም ምክንያት የግንባታዉ ሂደቱ ጥሩ ደረጃ ላይ መድረሱን በመግለፅ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊንና አጠቃላይ የስትራቴጂክ አመራር አባላትን አመስግነዋል።
የቢሮ ሀላፊ ክቡር አቶ አዋሌ መሀመድ ተቋራጩ በፍጥነት ስራው ማጠናቀቅት ላይ ትኩረት እንዲያደርግና የክፊያ ሁኔታውም በተገቢዉ መንገድ እንደሚከናወን አመላክተዋል።
በመጨረሻም በዚህ ስራ ላይ እየተባበሩ ያሉትን በጎ ሕሊናና ቅን ልቦና ያላቸውን ከቢሮው ጋር አብረው የሚሰሩትን የቴክኖሎጂ ካምፓኒዎችን በማመስገን ህንጻው ሙሉ በሙሉ እስኪጠናቀቅ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርብዋል። የህንጻ ግንባታው በ90 ቀናት ከሚጠናቀቁ ፕሮጀክቶችና በእቅድ ከተያዙት ተግባራት ውስጥ መሆኑ ከግምት ውስጥ ገብቶ ተያያዥ በክ/ከተማውና በወረዳ የሚሰሩ ስራዎች በግዜ ታስበው ወደ ስራ እንዲገባ በማለት የእለቱን መርሃ ግብር ተጠናቋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments