የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖ...

image description
- In Training    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስራዎች አፈፃፀም ዉጤታማነት ለማረጋገጥ የክዋኔ ኦዲት ተከናወነ

ITDB፦ ሰኔ/2017 ዓ.ም

የክዋኔ ኦዲቱ ዓላማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ

ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ስራዎች አፈፃፀም ዉጤታማነት አጠቃላይ ሁኔታዎችን በተመለከተ መረጃዎችን መሰብሰብ መገምገም ሲሆን በአፈፃፀሙ ላይ ክፍተቶች ካሉ የችግሮቹን መንስዔዎች በመለየት ችግሮቹን ለማስወገድ የሚያስችል የማሻሻያ ሀሳብ ለመስጠት ነዉ።

የአፈፃፀም ዉጤታማነትና አጠቃላይ ሁኔታዎችን በተመለከተ የተሰበሰቡትን መረጃዎች የቢሮ ሃላፊ አቶ አዋሌ መሀመድና ም/ቢሮ ሀላፊዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች በተገኙበት በዝርዝር አቀርቧል።

የክዋኔ ኦዲቱ የሚያተኩረው ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ስራዉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ስራዎች አፈፃፀም ዉጤታማነት መገምገም ሲሆን የትኩረት አቅጣጫዎቹ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች በታቀደዉ ዕቅድ መሰረት ህግና አሰራር ተከትለው መከናወናቸውን ማጣራት፣ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት የተቋማትን ፍላጎት መሰረት በማድረግ መደራጀቱንና የተጠናከረ ክትትል መከናወኑን እንዲሁም ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጥ ድጋፍ መደረጉን እና ዉጤታማነት መገምገም ማጣራት፣ የኢንፎሜሽን ቴክኖሎጂ የሙያ ፈቃድ በወጣው ስታንዳርድ መሰረት መሰጠቱንና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በትብብር መሰራቱን ማጣራት ነዉ። በመሆኑም በተነሱ ሀሳቦች ላይ መሰረት ያደረገ ዉይይት ተከናውኗል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments