የአዲስ መሶብ ቴክኖሎጂ ማስፈፀሚያ ዕቅድ የስራ...

image description
- In Training    0

የአዲስ መሶብ ቴክኖሎጂ ማስፈፀሚያ ዕቅድ የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ያለበት ደረጃ ተገመገመ

ITDB፦ ሰኔ 6/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የሚከናወነው የአዲስ መሶብ ቴክኖሎጂ ማስፈፀሚያ ዕቅድ የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ያለበት ደረጃ ላይ መሰረት ያደረገ ግምገማ የተቋማት ICT ዳይሬክተሮች, የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከፍተኛ ባለሞያዎች እና አልሚ ድርጂቶች በተገኙበት ተካሄደ።

የዚህ እቅድ ዋና ዓላማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመጀመሪያ ዙር የአዲስ መሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለሚገቡት 13ቱ ተቋማት የICT መሰረተ ልማታቸዉ ያለበትን ችግር

በመቅረፍ እና ወሳኝ የሆኑትን ሲስተም ሶፍትዌሮችን በተለይም አዲስ መሶብ ውስጥ እንዲገቡ የተመረጡ አገልግሎቶች በኦንላይን መጠቀም እንዲቻል ማድረግ ሲሆን ከአርተፊሻል ኢንተለጀንስ

ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ሲስተሞች እንዲተሳሰሩ ማድረግ እንዲሁም በፌዴራል የለሙትን ሲስተሞች ለአዲስ መሶብ በሚሆን መልኩ እንዲተገበር ማድረግ ነዉ።በዚህም የዕቅድ አፈፃፀም ቅድመ ሁኔታዎች፣ በመጀመሪያ ዙር ወደ ማዕከሉ የሚገቡ ተቋማት፣ ከኢትዩጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት (EAII) ጋር በመተባበር የሚሰሩ ተግባራት፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ጋር በመተባበር የሚሰሩ ተግባራት፣ መሰራት ያለባቸዉ ዋና ዋና ተግባራት፣ ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ የሚኖር አደረጃጀት፣ ክትትልና ድጋፍ የሚደረግበት አግባብ፣ የሪፖርትና ግምገማ አግባብና የድርጊት መርሃግብር በስማርት ሲቲ ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን ማብራርያ ተሰጥቶባቸዋል።

በመጨረሻም የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን የሌሎችን ሀገራት ተሞክሮ በመዉሰድ የተሰራ ፕሮጀክት መሆኑን ገልፀዉ የተቋማት ICT ዳይሬክተሮች, የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከፍተኛ ባለሞያዎች እና አልሚ ድርጂቶች ተቀናጅተው መስራት እንዲችሉ ምቹ የስራ ቦታ እና ሎጂስትክ የተዘጋጀ መሆኑንና በተቀመጠዉ ዕቅድ መሰረት የሚጠበቅብንን በአግባቡ ማከናወን እንደሚገባ በማመላከት መርሃ-ግብር ተጠናቋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments