የአዲስ አበባ ከተማን የትራንስፖርት ሴክተር ለማ...

image description
- In Training    0

የአዲስ አበባ ከተማን የትራንስፖርት ሴክተር ለማዘመን በተጀመሩት ፕሮጀክቶች ላይ ውይይት ተካሄደ

ITDB፦ ሰኔ 6/2017

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የከተማዋን የትራንስፖርት ሴክተር ለማዘመን ተጀምረው ባሉት ፕሮጀክቶች ላይ ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱም የሁለቱ ቢሮዎች አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን የተጀመሩት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ወደ ስራ በሚገቡበት አግባብ ላይ ትኩረት ያደረገ ነዉ።

በወይይቱም ላይ የትራንስፖርት ሴክተሩን ማዘመን ረገድ ምን እየተከናወነ እንዳለ ገለፃ የተደረገ ሲሆን በቀረበው ገለፃ ላይ መሰረት ያደረገ ወይይት ተደርጓል። በዚህም ውይይት ላይ የትራንስፖርት ቢሮ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወርቁ የትራንስፖርት ዘርፍ ችግሮች በቴክኖሎጂ በመታገዝ በአግባቡ እንዲፈቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እገዛ እንደሚያስፈልግ ገልፀዉ የሲቲ ባስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አካሉ አሰፋ የትራንስፖርትን ማነቆ በቴክኖሎጂ መፍታት እንዳለበት፣ ከዬትኛውም ዘርፍ በበለጠ የቴክኖሎጂ ድጋፍ እንደሚሻ አመላክተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የስማርት ሲቲ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን ከተማን ለማዘመን ትራንስፖርት ቢሮን መደገፍ አስፈላጊ መሆኑንና የቢሮ ድጋፍ መፈለጋቸውን አግባብ መሆኑን ገልፀዉ የነበሩ ክፍተቶችን በመሙላት በማያዳግም መልኩ በትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባና ይሄንን ሴክተር መደገፍም አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አዋሌ መሐመድ የትራንስፖርት ዘርፉን ችግር ለመፍታት መሟላት ያለባቸውን ግብአቶች የትራንስፖርት ቢሮ ማሟላት እንደሚገባዉ እና ቀሪዎችን ስራዎች የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስራ መሆኑን ገልፀው ከስማርት ሲቲ ስድስት አምዶች መካከል ስማርት ሞቢሊቲ አንዱ በመሆኑ አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ ቲም በማዋቀርና በብርቱ መንፈስ ወደ ስራ መግባት እንደሚገባ አመላክዋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments