በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖ...

image description
- In Technology Trends    0

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖለጂ ልማት ቢሮ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የ5ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠና ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ

ITDB፦ ሰኔ 2/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ባዘጋጀው የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ላይ ትኩረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖለጂ ልማት ቢሮ ተሰጠ። በዚህ መርሃ ግብር ላይ የጤና ቢሮ ሃላፊ፣ ምክትል ምክትል ቢሮ ሃላፊዎች፣ የማኔጅመንት ኣባላትና ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን የመርሃ ግብሩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ ሃገራችን የጀመረችውን የዲጂታል ቴክኖሎጂ አገልግሎት ውጤታማ ለማድረግ ሠራተኛው የኢትዮ ኮደርስ ኢነሼቲቭ ስልጠና በበየነ መረብ በመውሰድ እራሱን ለማብቃትና ስኬታማ ለማድረግ መትጋት አለበት ሲሉ ሀሳባቸዉን ገለፀዋል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስማርት ሲቲ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን የስማርት ሲቲን ስድስቱን ምሰሶዎች የዳሰሱ ሲሆን በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የሚካተቱትን አራቱን ኮርሶች ማለትም ዌብ ፕሮግራሚንግ፣ አንድሮይድ ፕሮግራሚንግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ መሆናቸውን ጠቅሰዉ የትምህርትን ጥቅም በመግለፅም ወጣቶቻችን ሳይዘናጉ መማር እንደሚገባቸዉ አመላክተዋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments