የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ዉይይት ተካሄደ
ITDB፦ ጥር 6/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የዉይይት መርሃ ግብር ተካሄደ።
በዉይይት መርሃ ግብሩ የቢሮ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎች፣ ባለሙያዎች፣ የክ/ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን መሪዎችና የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን የመርሃ ግብሩ ዋና ዓላማ ቢሮዉ በ2018 በጀት ዓመት በግማሽ ዓመት ለማከናወን በዕቅድ የያዛቸውን ቁልፍ ዓበይት ተግባራት አፈፃፀም የደረሰበትን ደረጃ እንዲሁም አፈፃፀም ሂደት የነበሩ ጥንካሬዎችና ድክመቶች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና ችግሮችን ለመፍታት የተሄደበት ርቀት በጥቅል መዳሰስና መተንተን ላይ ትኩረት ያደረገ ነዉ።
የመርሃ-ግብሩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዉ በዛሬዉ መርሃ ግብር የግማሽ ዓመት እቅድ ሪፖርት በመገምገም በቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸዉ የሚገባቸዉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በጋራ አቅጣጫ ማስቀመጥ መሆኑን በማመላከት መርሃ ግብሩን በይፋ አስጀምረዋል።
የቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተዉ የቁልፍ ተግባራት አፈፃፀም፣ የአበይት ተግባራት አፈፃፀም፣ የታዮ ጥንካሬዎች፣ ድክመቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች የተወሰዱ መፍትሔዎች ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል። በተያያዘም የቀረበዉ ሪፖርት ላይ መሰረት ያደረጉ ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች የተነሱ ሲሆን የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድና የዘርፍ ሀላፊዎች አስተያየቶችን እንደ ግብአት በመዉሰድ ለጥያቄዎቹ ምላሽ ሰጥተዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments