የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ተገመገመ
ITDB፦ ጥር 5/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ተገመገመ።
በግምገማው የቢሮ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎችና ከፍተኛ ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን የመርሃ ግብሩ ዓላማ ቢሮዉ የ2018 በጀት ዓመት በግማሽ ዓመት ለማከናወን በዕቅድ የያዛቸውን ቁልፍ ዓበይት ተግባራት አፈፃፀም የደረሰበትን ደረጃ እንዲሁም አፈፃፀም ሂደት የነበሩ ጥንካሬዎችና ድክመቶች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና ችግሮችን ለመፍታት የተሄደበት ርቀት በጥቅል መዳሰስና መተንተን ላይ ትኩረት ያደረገ ነዉ።
የቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተዉ የቁልፍ ተግባራት አፈፃፀም፣ የአበይት ተግባራት አፈፃፀም፣ የታዮ ጥንካሬዎች፣ ድክመቶ፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች የተወሰዱ መፍትሔዎች ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል። በተያያዘም የቀረበዉ ሪፖርት ላይ መሰረት ያደረጉ ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች የተነሱ ሲሆን የቢሮ አመራሮችና የሚመለከታቸዉ የስራ ክፍሎች ምላሽ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የቀረበው ሪፖርት ጥሩ የስራ እንቅስቃሴዎች እንዳሉ የሚያሳይ መሆኑንና ነገር ግን እንደክፍተት የተነሱ ሀሳቦች ላይ ጠንክረን በመስራት ትልቅ ለዉጥ ልናመጣ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments