ከተማ አቀፍ የኢትዮ ኮደርስ የእውቅናና ማነቃቂያ መርሃ-ግብር ተካሄደ
ITDB፦ ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከተማ አቀፍ የኢትዮ ኮደርስ የእውቅናና ማነቃቂያ መርሃ-ግብር ተካሄደ።
በመርሃ-ግብሩ የቢሮ አመራሮች፣ በም/ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀንበሩ፣ በም/ከንቲባ ማዕረግ የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማትዮስ፣ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን፣ የት/ት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ፣ የቋሚ ኮሚቴ አባላትና የኮሌጅ ዲኖች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የመርሃ-ግብሩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈው መዲናችን በማያቋርጥ የለውጥ ሂደት ላይ መሆኑዋንና ለዚህም የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስልጠና የጎላ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልፀው ወጣቱን ትውልድ በዲጂታል ኢኮኖሚ ተሳታፊ ለማድረግ እንዲሁም ተወዳዳሪ የሆነ ትውልድ ለመፍጠር የጠቅላይ ሚኒስቴራችን ኢኒሼቲቭ የሆነው አምስት ሚሊዮን ኢትዮ-ኮደርስ ትልቅ አስተዋጽኦ አንዳበረከተ አመላክቷል፡፡ አያይዘውም ቢሮው ከፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ፣ ት/ት ቢሮ፣ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እና ስራና ክህሎት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በከተማ ደረጃ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ መሆኑን አንዲሁም በቀጣይ በኢትዮ-ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የተሻለ አፈጻጸም ለማምጣት በባለቤትነት መንፈስ መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
የቢሮ ስማርት ሲቲ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አጭር መረጃና ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ሪፖርቱም ስለ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ ስለ ስሉጥ ከተማ ምንነትና ራዕይ፣ የስሉጥ ከተማ ስድስት አምዶችና በአምዶቹ ስር የለሙ ሲስተሞችና ኢንፍራስትራክቸሮች፣ የኢትዮ-ኮደሮች አላማና አስፈላጊ ገፆች እንዲሁም የኮሚኒኬሽን ቻናል ዝርዝር ማብራሪያ ሰተዋል፡፡
በተያያዘም ለሰራተኞቻቸው የተሻለ ግንዛቤ የፈጠሩና ስልጠናውን በተገቢ መንገድ ላስተባበሩ እንዲሁም ፕሮግራሙን በብቃት የተከታተሉና የበቁ ሰልጣኞች የእውቅናና የሽልማት መርሃ- ግብር የተካሄደ ሲሆን በመጨረሻም በም/ክንቲባ ማዕረግ የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ በ2025 ውጤታማ ተግባራትን ፈጽመን ወደ ዲጂታል 2030 መግባታችን እውን መሆኑን ገልፀው በቴክኖሎጂ ረገድ ያለውን አመርቂ ውጤት ለማገዝ በጠቅላይ ሚኒስቴራችን አማካኝነት እየተካሄደ ያለውን አምስት ሚሊዮን ኢቲዮ-ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ትልቅ ሚና እንዳለው አመላክተዋል፡፡ በመሆኑም ፕሮግራሙን በመመዝገብና በመሰልጠን አገራዊ አደራችንን እንወጣ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments