ለአድዋ ሙዝየም የለማዉ web based application ተገመገመ
ITDB፦ ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከASTU ጋር በጋራ በመሆን ለአድዋ ሙዝየም ያለሙት web based application ተገመገመ።
የመርሃ-ግብሩ ዋና ዓላማ መተግበሪያ ያለበትን ሁኔታ በመገምገም መካተት ያለባቸዉን ተግባራት ላይ ምክረ ሀሳብ መስጠት ሲሆን የለማዉ web based application ስለአድዋ ድል መታሰቢያ ታሪክ፣ ፈጣን የትኬት ግዢ፣ ሁነቶችን ለመመልከትና የሙዝየሙን አጠቃላይ አገልግሎት በዝርዝር የያዘ ነዉ። በመሆኑም በግምገማዉ ወቅት መተግበርያዉ በርካታ ተግባራትን ያካተተ መሆኑንና ለተገልጋዮች ምቹ መሆኑ የገለፀ ሲሆን በተጨማሪም መካተት የሚገባቸውን ርዕሰ ጉዳዮችን በማመላከት መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments