በመልካም አስተዳደር ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና...

image description
- In Technology Trends    0

በመልካም አስተዳደር ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ተሰጠ

ITDB፦ ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም

ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሰራተኞች በመልካም አስተዳደር ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ተሰጠ።

ስልጠናው በለዉጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አማካኝነት የተሰጠ ሲሆን የቢሮ ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል። የስልጠናው ዋና ዓላማ ለተቋሙ ሰራተኞች ስለመልካም አስተዳደር ምንነትና መርሆዎች እንዲሁም መልካም አስተዳደር በኢትዮጵያ ያለበት ሁኔታ ምን እንደሚመስል ግንዛቤ መፍጠር ላይ ትኩረት ያደረገ ነዉ።

የስልጠናውን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ነብዩ ፍቃዱ ስልጠናዉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመለየትና ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚረዳ ገልፀዉ ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ስራ ላይ ማዋል እንደሚገባ በመጠቆም መልካም የስልጠና ግዜ ተመኝተዋል።

ስልጠናዉን የሰጡት የለዉጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ በዳሶ ገለቶ የመልካም አስተዳደር ምንነት፣መልካም አስተዳደር በኢትዮጵያ፣ የመልካም አስተዳደር መርሆዎች፣ የተለያዩ ሀገራት መልካም አስተዳደርን በማስፈን ረገድ ያላቸው ተሞክሮ፣ የመልካም አስተዳደር መለያ መስፈርትና የዕቅድ ማዘጋጃ እንዲሁም ሪፖርት ቢጋር ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ከዚህም ጋር በተያያዘ ስልጠናዉ ላይ መሰረት ያደረጉ ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች የተነሱ ሲሆን የለዉጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ግርማ ከበደ ተገቢዉን ምላሽ በምሳሌ በማስደገፍ ተሰጥተዋል።

በመጨረሻም የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተዉ የስልጠናው ቆይታ ጥሩ እንደነበርና ያደጉት ሀገራት መልካም አስተዳደር በማስፈን ረገድ ያላቸዉን ተሞክሮ ወደ እኛ ማምጣት እንደሚገባ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ምንነትና መርሆዎች ላይ ግንዛቤያችንን በማሳደግ ተቋማችንን ብሎም ሀገራችንን አንድ ደረጃ ከፍ ማድረግ እንደሚገባ በማመላከት ስልጠናውን ላዘጋጁ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

#AddisSmartcity

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments