በአገልግሎት አሰጣጥና በተግባቦት ክህሎት ላይ መሰረት ያደረገዉ ስልጠና ተጠናቀቀ
ITDB፦ ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በአገልግሎት አሰጣጥና በተግባቦት ክህሎት ላይ መሰረት ያደረገ ስልጠና ተጠናቀቀ።
የስልጠናው መዝጊያ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተዉ ስልጠናው ክህሎታችንንና ስራ ላይ ያለንን አቅም የምናሳድግበት መሆኑንና ከዚህም ባሻገር የሚሰጡንን የኢኒሼቲቭ ስራዎች በብቃት የምንወጣበት መሆኑን ገልፀዉ ስልጠናዉን በአግባብ መከታተላችንን በቀጣይ የምናከዉናቸዉ ስራዎች ላይ በግልፅ እንደሚታይ በማመላከት ስልጠናዉን ላዘጋጁ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ስልጠናዉ በሰዉ ሀብት ዳይሬክቶሬት አማካኝነት በሁለት ዙር የተካሄደ ሲሆን የስልጠናዉ ዋና ዓላማ ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥን እና የተግባቦት ክህሎት ፅንሰ ሀሳብ ላይ የተሻለ መረዳት በመፍጠር የአገልግሎት አሰጣጥና የተግባቦት ክህሎት ተግዳሮቶች የመለየትና ማሻሻል ስልቶች የመደገፍ ክህሎት ማዳበር ማሳደግ እንዲሁም በተገልጋይ አያያዝና ቅሬታ አፈታት ዙርያ የተሻለ ክህሎት እንዲኖር ማድረግ ነዉ።
ስልጠናዉን ያዘጋጁት የሰዉ ሀብት ዳይሬክተር ወ/ሪት ፀሀይ በዳዳ የአገልግሎት አሰጣጥ ፅንሰ ሀሳብ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ መርሆዎች፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ስልቶችና ዉጤታማ የተግባቦት ክህሎት ላይ ሰፊ ጥልቅ የሆኑ ማብራሪያ የሰጡትን አሰልጣኞች አመስግነዉ የተቋሙ ሰራተኞች ስልጠናዉን በጥብቅ ዲሲፕሊን በመከታተላቸዉ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments