የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የ...

image description
- In Training    0

የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዘርፎች ዓበይት ተግባራት አፈፃፀም ሪፖርት ቀረበ

ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዘርፎች ዓበይት ተግባራት አፈፃፀም ሪፖርት ቀረበ።

በመርሃ-ግብሩ የቢሮ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች የተገኙ ሲሆን የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ በሪፖርቱ በዝግጅት ምዕራፍ የተከናወኑ ተግባራትና በቀጣይ ስድስት ወራት መከናወን ስለሚገባቸው ተግባራት በየዘርፉ የሚቀርብ መሆኑንና ብዥታ የሚፈጥሩ ነገሮች ካሉ በዳይሬክተሮች አማካኝነት ምላሽ በመስጠት የማጥራት ተግባር እንደሚከናወን ገልፀዋል።

በተያያዘም የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመርያ ግማሽ ዓመት ዓበይት ተግባራት ሪፖርት ስማርት ሲቲ ዘርፍ፣ መሰረተ ልማት ዘርፍ፣ ኦፕሬሽንና ጥገና አገልግሎት ዘርፍ የቀረበ ሲሆን በቀረበዉ ሪፖርት ላይ መሰረት ያደረጉ ጥያቄዎችን እንደግብአት በመዉሰድ በሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ተሰጥቶበታል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments