የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ

image description
- In Training    0

የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ

ITDB፦ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሳምንታዊው የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡ በዚህ መርሃ ግብር ላይ የቢሮው አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ ባለፈዉ ሳምንት በርካታ ተግባራትና የቴክኖሎጂ ሽግግር መርሃ-ግብር መካሄዱን ገልፀዉ የዛሬዉ ወርቃማ ሰኞ የእዉቀት ሽግግር መርሃ ግብር የተግባቦት ክህሎታችንን የምናዳብርበት እንዳሁም ለእለት ተእለት እንቅስቃሴያችን የሚጠቅም መሆኑን በማመላከት መልካም ጊዜን ተመኝተዋል።

የእዉቀት ሽግግሩን ያደረጉት የቴክኖሎጂ ሽግግር ቡድን መሪ አቶ ይድነቃቸዉ ተስፋዬ ስኬታማ ተግባቦት በሚል ርዕስ ስር የተግባቦት ምንነት፣ የተግባቦት ፍሰት፣ የተግባቦት ስርዓት፣ የተግባቦት አይነቶች፣ ንግግር አልባ ተግባቦት፣ ስኬታማ ተግባቦት በተመለከተ ትኩረት ሊሰጣቸዉ የሚገባቸዉ ነገሮች፣ የዉጤታማ ተግባቦት መገለጫ ባህሪዎች፣ ስኬታማ ተግባቦት የሚያካትታቸዉ ነገሮች ላይ ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም የቢሮ ሀላፊ የእዉቀት ሽግግሩ መልካም እንደነበርና ስኬታማ ስነ-ተግባቦትን በተመለከተ የነበራቸዉ ተሞክሮ ያካፈሉ ሲሆን በሳምንቱ የሚከናወኑ ተግባራት ዝርዝር በማመላከት መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments