የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የመማክርት ጉባ...

image description
- In Training    0

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የመማክርት ጉባኤ ተቋቋመ

ህዳር 25/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከተገልጋዬች ጋር ለመስራት በየተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶች ለማሻሻልና ዉጤታማ ለማድረግ እንዲቻል ከከተማ አስተዳደሩ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ ባወረደዉ መመርያ መሰረት በተቋም ደረጃ የመማክርት ጉባኤ ተቋቋመ።

በጉባኤው የቢሮዉ አመራሮች የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን የመርሃ ግብሩ ዋና ዓላማ በከተማ ደረጃ አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ተገልጋዮች፣ ባለድርሻ አካላት፣ የመንግስት ተቋማት እና የልማት ድርጅቶች ከቢሮ ጋር በመሆን የሚጠበቅባቸዉን ሚና በዉጤታማነት እንዲመጡ የሚያግዝ የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት ነዉ።

የመርሃ ግብሩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዉ የዛሬዉ መርሃ ግብር ዓላማ አገልግሎቶችን ለማሻሻልና ክፍተቶችን በማረም ዉጤታማ የሆነ ፈጣንና ቀልጣፋ ፍትሀዊ የአሰራር ስርዓት መፍጠር ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

በተያያዘም "የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ" ማቋቋምና ትግበራ ማንዋል ላይ የተዘጋጀዉን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሰጡት የፐብሊክ ሰርቪስ ስታንዳርዳይዜሽን ምዘና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ይመር የሰነዱ አስፈላጊነት፣ ለሰነድ ዝግጅት መነሻ ሁኔታዎች፣ የሚቋቋመው የመማክርት ጉባኤ ጠቀሜታ፣ የመማክርት ጉባኤ የቆይታ ግዜ፣ መማክርቱ ወደ ተግባር ከገባ በኃላ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ ተግባርና ሀላፊነት፣ በየተቋሙ የሚደራጀዉ መማክርት ጉባኤ አጋዥ አካላት፣ የሲቪክ ማህበራት ሚና፣ የመማክርት ጉባኤ የግንኙነት ሁኔታ፣ የመማክርት ጉባኤ መርሆችና የመማክርት ጉባኤ ዕቅድ ዝግጅት በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን በመጨረሻም ጠቅላላ ጉባኤና ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መርጦ በማፅደቅ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments