ሳምንታዊው የወርቃማ ሰኞ የዕውቀት ሽግግር መርሃ...

image description
- In Training    0

ሳምንታዊው የወርቃማ ሰኞ የዕውቀት ሽግግር መርሃ ግብር ተከናወነ

ህዳር 8/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሳምንታዊው የዕውቀት ሽግግር መርሃ ግብር ተከናወነ። በዚህ መርሃ ግብር ላይ የህይወት ውጣ ውረድና ስኬት በሚል ርእስ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የስማርት ሲቲ ዘርፍ ም/ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን የዕዉቀት ሽግግር ያደረጉ ሲሆን የቢሮ ሃላፊዎች፣ ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎችና ሠራተኞች ተሳትፈውበታል።

ዶ/ር ቱሉ በርዕሳቸው ውስጥ ማንም ሰው ያለምንም ፈተናና ዉጣዉረድ ስኬት ላይ ሊደርስ እንደማይችል፣ በነገሮችና በሰዉ ተግባር ላይ ቸኩለን መፍረድ እንደማይገባ፣ የራሳችንን አቅምና ብቃት የማወቅ አስፈላጊነትን፣ በመጥፎ ልማድ መወሰን እንደሌለብን፤ እንዲሁም በህይወታችን በምንም ነገር ተስፋ መቁረጥ እንደሌለብን በምሳሌዎች በማስደገፍ ገልፀዉ ስኬት በጥሩ ሁኔታ የተዘጋጀ ዕቅድና በፅናት የመስራት ውጤት መሆኑንም ጠቁመዋል።

በመጨረሻም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ አዋሌ መሐመድ በርእሱ ላይ መሰረት በማድረግ በምንም ሁኔታ ውስጥ ተስፋ መቁረጥ እንደማይገባ ገልፀው መልካም የስራ ሳምንት በመመኘት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments