የICT መሳርያዎች እና እቃዎችን ጠግኖ መልሶ በ...

image description
- In Training    0

የICT መሳርያዎች እና እቃዎችን ጠግኖ መልሶ በመጠቀም የመንግስት ሃብት የማዳን ስራ ንቅናቄ ማስጀመርያ መርሃ ግብር ተካሄደ

 

ITDB፦ ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ጋር በመሆን በከተማ አስተዳደሩ ስር ባሉ ተቋማት ተበላሽተዉ የተቀመጡ የICT መሳርያዎች እና እቃዎችን ጠግኖ መልሶ በመጠቀም የመንግስት ሃብት የማዳን ስራ ንቅናቄ ማስጀመርያ መርሃ ግብር ተካሄደ።

በመርሃ ግብሩ የክ/ከተማና ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቡድን ICT ባለሙያዎችና የሚመለከታቸው አካላት የተገኙ ሲሆን በ2017 ዓ.ም በየተቋማቱ የነበሩ 4,693 የአይሲቲ እቃዎች እንዲጠገኑ ከአዲስ አበባ መንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን በተጠየቀዉ መሰረት ከዚያ በላይ እቃዎችን ጥገና በማድረግ ከ130 ሚሊዮን ብር በላይ ለማዳን መቻሉ ይታወሳል። በመሆኑም በ2018 ዓ.ም ይህንን መሰል ተግባር ለማስቀጠል ያስችል ዘንድ ይህን የንቅናቄ ማስጀመርያ መርሃ ግብር ተከናውኗል።

የመርሃ-ግብሩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ኦፕሬሽንና ጥገና አገልግሎት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ዳኛቸዉ ፈለቀ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዉ በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ከተከናወኑ ትልልቅ ተግባራት መካከል የመንግስትን ንብረት ከብክለት ማዳን መሆኑን ገልፀዉ ይህ ተግባር ዛሬን ብቻ ሳይሆን ለመጪዉ ትዉልድ መሰረት የሚሆን ትልቅ ተግባር በመሆኑ ቢሮዉ እገዛ በሚሹ ጉዳዮች ላይ ከጎናቸዉ እንደሆነ አመላክተዋል።

ቢሮዉ ከመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ጋር በመሆን በ2018 ዓ.ም የICT እቃዎች ጥገናን በተመለከተ የተዘጋጀውን ሰነድ ያቀረቡት የሀርድዌር ቡድን መሪ አቶ ይግረማቸዉ ማሞ የስራዉ ስፋት፣ የቡድን አወቃቀርና የግዜ ሰሌዳዉን በተመለከተ ዝርዝር ማብራርያ የሰጡ ሲሆን ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች የኦፕሬሽን አገልግሎት ዘርፍ ዳሬክተርና የሀርድዌር ቡድን መሪ ምላሽ በመስጠት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments