በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖ...

image description
- In Training    0

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት የቅንጅታዊ አሰራር ሪፖርት ቀረበ

ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም

በመርሃ ግብሩ የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ፣ የተቋማት ተወካዮችና የሚመለከታቸዉ አካላት የተገኙ ሲሆን የመርሃ ግብሩ ዓላማ ስታንዳርዳቸዉን የጠበቁ የሲስተም ልማትና አገልግሎት እንዲፈጠር ለማድረግ ምቹ የስራ አካባቢን ለመፍጠር ቢሮዉ ተልኮዉን እዉን ለማድረግ በቅንጅት እየሰራ በመሆኑ አንደኛ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም በቀጣይ መከናወን ያለባቸዉ ተግባራት ላይ አቅጣጫ ማመላከት ነዉ።

በመሆኑም የ2018 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት የቅንጅታዊ አሰራር ሪፖርት ያቀረብህ የሪፎርም ዳይሬክተር አቶ ግርማ ከበደ የትስስር ሰነዱ ሁኔታ፣ የትስስር ሰነዱ አስፈላጊነት፣ የትስስር ሰነዱ መርሆዎች፣ የትስስር ሰነዱ ወሰንና የተሰሩ ዋና ዋና ተግባራት እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮችን በዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም በቀረበዉ ሰነድ ላይ መሰረት ያደረገ ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄ ከተሳታፊዎች የተነሱ ሲሆን የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተዉና የሪፎርም ዳይሬክተር ምላሽ በመስጠት መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments