"የሳይበር ደህንነት የዲጅታል ኢትዮጵያ መሰረት" በሚል መሪ ቃል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ITDB፦ ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ 6ተኛዉ ሀገር አቀፍ የሳይበር ወርን በማስመልከት "የሳይበር ደህንነት የዲጅታል ኢትዮጵያ መሰረት" በሚል መሪ ቃል ለቢሮ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
የስልጠናው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ስማርት ሲቲ ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን በመዲናችን የስማርት ሲቲ ፅንሰ ሀሳብን እየተገበርን መሆኑንና ከተማችንን ብሎም ተቋማችንን ከሳይበር ደህንነት ስጋት ለመጠበቅ ግንዛቤያችንን በማሳደግ ተጋላጭነታችንን ልንቀንስ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በተያያዘም የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የሳይበር ሰኪዮሪቲ ስልጠና ሀገራችን ያለችበትን የማያቋርጥ ዲጅታል ቴክኖሎጂ ደህንነት ለመጠበቅና ጠንቃቃ ማህበረሰብን ለመገንባት ወሳኝ ሚና እንዳለዉ ገልፀዉ ለዚህ ስልጠና መሳካት የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን በማቅረብ ስልጠናዉን በይፍ አስጀምረዋል።
ስልጠናዉን የሰጡት የINSA የሳይበር ገቨርናነስ ክፍል ባለሙያ አቶ መሰረት ስለሳይበር ምህዳር ምንነትና የሳይበር ጥቃት ማለት ምን ማለት ነዉ የሚለዉን ገልፀዉ Ethiopia global standard, global cyber threats landscape, ket threats, national cyber attack threats, key challenge, Recommendation national frameworks ላይ በምሳሌ በማስደገፍ ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋልኀ።
በመጨረሸም ስልጠናዉ ላይ መሰረት የደረጉ ሀሳብ አሰተያየትና ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች የተነሱ ሲሆን አሰልጣኙ ምላሽ ሰጥተዉበታል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments