የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ

image description
- In Training    0

የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ

ITDB፦ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሳምንታዊው የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡ በዚህ መርሃ ግብር ላይ የቢሮው አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች እና ባለ ሙያዎች የተገኙ ሲሆን የኦፕሬሽንና አገልግሎት ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ ድርሻዬ ካሰኝ የልማድ ሀይል በሚል ርዕስ ስር፣ አቶማክ ልማድ ምንድነዉ፣ የልማድ ኡደት ምንድነዉ፣ ጥሩ ልማድ እንዴት እናዳብር፣ የጥሩ ልማድ ጥቅሞች፣ የልማድ አራቱ ህጎች ላይ ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል።አያይዘዉም ትንንሽ ለዉጦች በማምጣት የየዕለት ዉሳኔዎችን ላይ ትልልቅ ዋጋ ያላቸዉ ልማዶችን ማምጣት እንደምንችልና ምንአልባት አንድ ቀን ላይሳካ ይችል ይሆናል ነገር ግን ሁለተኛ አትፍቀዱለት ሲሉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ በቅዳሜና ዕሁድ መርሃ ግብር የአንደኛ እሩብ ዓመት ግምገማ መካሄዱንና እንደ ከተማ አስተዳደር በርካታ ጥያቄዎች መነሳታቸዉን ገልፀዉ እንደ ቢሮ በርካታ ስራዎች ከእኛ እንደሚጠበቅና የመጀመርያ ሩብ ዓመት አፈፃፀማችን ጥሩ እንደነበርና ነገር ግን የማህበራዊ ማዲያ አጠቃመማችንን ማሳደግ እንዳለብን በማመላከት መልካም የስራ ጊዜን ተመኝተዋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments