development technology ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና መጠናቀቁን አስመልክቶ የመዝጊያ መርሃ ግብር ተካሄደ
ጥቅምት 7/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴከኖሎጂ ልማት ቢሮ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለቢሮ ሶፍትዌር ፕላትፎርም ልማት እና ኦፕሬሽንና ጥነና ዳይሬክቶሬት አስራ አምስት ባለሙያዎች development technology ላይ ትኩረት ያደረገ የአምስት ቀን ስልጠና መስጠቱ ይታወሳል፡፡ የስልጠናዉ ዋና ዓላማ የሰዉ ሀይልን በማብቃት በውስጥ አቅም ሶፍትዌር የማበልዕግ ስራ በመስራት የመንግስት ሀብትን ከብክነት ማዳንና ፈጣንና ቀልጣፋ ፍትሐዊ አገልግሎት መስጠት ላይ ትኩረት ያደረገ ነዉ። ስልጠናዉን ሲሰጡ የነበሩ አሰልጣኞች ሰልጣኞች ጥሩ ተሳትፎ እንደነበራቸዉና በቀጣይም አቅማቸዉ ማሳደግ የሚችሉበት የማህበራዊ ሚዲያ ቻናሎች እንደጠቆሟቸዉ እንዲሁም ድጋፍ በሚሹ ጉዳዬች ዩኒቨርሲቲዉ ከጎናቸዉ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ ስለ ስልጠናዉ አስፈላጊነት ገልፀዉ ዩኒቨርሲቲው ስላደረገዉ ቀና ትብብር በቢሮዉ ስም በማመስገን በቀጣይም ይህንን መሰል ተግባራትን አጠናክሮ በመቀጠል በአብሮት ወደፊት ልንጓዝ ይገባል ሲሉ ሀሳባቸዉን ገልፀዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments